አዲስ አበባ፣ ጥር 8፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ15ኛ ሳምንት ሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ነገሌ አርሲ እና ወላይታ ድቻ 1 ለ 1 አቻ ተለያይተዋል።
ቀን 9 ሰዓት ላይ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ የነገሌ አርሲን ግብ ገ/መስቀል ዱባለ ሲያስቆጥር÷ የወላይታ ድቻን ካርሎስ ዳምጠው በፍጹም ቅጣት ምት ከመረብ አሳርፏል።
ቀደም ሲል ቀን 7 ሰዓት ላይ በአዲስ አበባ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ሸገር ከተማ እና ፋሲል ከነማ ያለምንም ግብ አቻ ተለያይተዋል።
በአዲስ አበባ ስታዲየም ከቀኑ 10 ሰዓት ጀምሮ ሀዲያ ሆሳዕናን ከምድረ ገነት ሽረ ያገናኘው ጨዋታ የመጀመሪያው አጋማሽ 1 ለ 1 በሆነ ውጤት ወደ መልበሻ ክፍል አምረተዋል።
እንዲሁም በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም አመሻሽ 12 ሰዓት ላይ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጨዋታውን ያደርጋል።