አዲስ አበባ፣ ጥር 9፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የሸኮ ብሔረሰብ የዘመን መለወጫና የምስጋና በዓል “ቲከሻ ቤንጊ” በአዲስ አበባ በተለያዩ መርሐ ግብሮች ተከበረ፡፡
በዓሉ የመንግሥት ስራ ኃላፊዎች፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት፣ የብሔረሰቡ ተወላጆች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ነው በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር አዳራሽ የተከበረው።
በመድረኩ በተለያዩ ምሁራን ጥናታዊ ጽሑፎችን አቅርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል።
በበዓሉ መሰረት የሸኮ ብሔረሰብ ወቅቱ ምርት ተሰብስቦ ወደ ጎተራ የሚገባበት መሆኑን ተከትሎ ያመረተውን ይዞ አምላኩን የሚያመሰግንበት እንደሆነም ተመላክቷል።
በአሸናፊ ሽብሩ