አዲስ አበባ፣ ጥር 9፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ22ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ማንቼስተር ዩናይትድ ማንቼስተር ሲቲን 2 ለ 0 አሸንፏል።
በኦልድትራፎርድ ስታዲየም በተካሄደው የማንቹርያን ደርቢ ጨዋታ የቀያዮቹን ግቦች ብሪያን ምቡሞ እና ፓትሪክ ዶርጉ ከመረብ አሳርፈዋል።
በጨዋታው ላይ ማንቼስተር ዩናይትድ ብልጫ ወስዶ የተጫወተ ሲሆን÷ ማንቼስተር ሲቲ ደግሞ ደካማ የማጥቃት እንቅስቃሴ አድርጓል።
በዚህ 198ኛው የማንቼስተር ደርቢ ጨዋታ በዩናይትዶች አሸናፊነት ተጠናቅቋል።
በሊጉ 10ኛ ድሉን ያስመዘገበው ዩናይትድ በ35 ነጥብ ደረጃውን ከ7ኛ ወደ 4ኛ ከፍ አድርጓል።
በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ 5ኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ማንቼስተር ሲቲ በ43 ነጥብ ሁለተኛ ደረጃን ይዞ ከሊጉ መሪ አርሰናል ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት የማጥበብ እድል አምክኗል።
የሊጉ መርሐ ግብር ቀጥሎ ሲካሄድ ምሽት 2፡30 ላይ መሪው አርሰናል ከኖቲንግሃም ፎረስት ይገናኛል።