ስፓርት

አርሰናል እና ኖቲንግሃም ፎረስት አቻ ተለያዩ

By Yonas Getnet

January 17, 2026

አዲስ አበባ፣ ጥር 9፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ22ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር አርሰናል እና ኖቲንግሃም ፎረስት 0 ለ 0 ተለያይተዋል።

ምሽት 2፡30 ላይ የተካሄደው የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ ያለምንም ግብ የተጠናቀቀ ሲሆን÷ አርሰናል በሊጉ በሁለተኛ ደረጃ ከሚከተለው ማንቼስተር ሲቲ ያለውን ልዩነት ወደ 9 ማስፋት የሚችልበትን ዕድል ሳይጠቀምበት ቀርቷል።

ቀደም ብለው በተደረጉ ጨዋታዎች ማንቼስተር ዩናይትድ ማንቼስተር ሲቲን እንዲሁም ቼልሲ ብሬንትፎርድን 2 ለ 0 ሲያሸንፉ ሊቨርፑል እና በርንሌይ 1 ለ 1 አቻ ተለያይተዋል።

በተጨማሪም ሰንደርላንድ ክሪስታል ፓላስን 2 ለ 1፣ ሊድስ ዩናይትድ ፉልሃምን 1 ለ 0 ሲያሸንፉ÷ ዌስትሀም ዩናይትድ ቶተንሃምን 2 ለ 1 መርታት ችለዋል።