ስፓርት

ሴኔጋል የአፍሪካ ዋንጫ ሻምፒዮን መሆኗን ተከትሎ የዛሬው ዕለት ብሔራዊ በዓል እንዲሆን አወጀች

By Mikias Ayele

January 19, 2026

አዲስ አበባ፣ ጥር 11፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ሴኔጋል የአፍሪካ ዋንጫ ሻምፒዮን መሆኗን ተከትሎ የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ባሲሩ ዲዮማዬ የዛሬው ዕለት ብሔራዊ በዓል እንዲሆን አውጀዋል፡፡

ሴኔጋል በሞሮኮ አስተናጋጅነት ሲካሄድ በቆየው 35ኛው የአፍሪካ ዋንጫ አዘጋጇን ሀገር ሞሮኮ በማሸነፍ በትናንትናው ዕለት የውድድሩ ሻምፒዮን ሆናለች፡፡

ድሉን ተከትሎ በዋና ከተማዋ ዳካር እና በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ሴኔጋላውያን ደስታቸውን እየገለጹ ይገኛሉ፡፡

የቴራንጋ አንበሶቹ እልህ አስጨራሽ በነበረው የፍፃሜ ጨዋታ ትናንት ምሽት ሞሮኮን በማሸነፍ በታሪካቸው ለ2ኛ ጊዜ የአፍሪካ ሻምፒዮን መሆን ችለዋል፡፡

ሴኔጋል በፈረንጆቹ 2021 የተዘጋጀውን 30ኛ የአፍሪካ ዋንጫ ባነሳችበት ወቅት የወቅቱ ፕሬዚዳንት ማኪ ሳል በተመሳሳይ ብሔራዊ የድል በዓል ማወጃቸው ይታወሳል፡፡

በሚኪያስ አየለ