የሀገር ውስጥ ዜና

የጥምቀት በዓል በስኬት ተጠናቀቀ

By Adimasu Aragawu

January 19, 2026

አዲስ አበባ፣ ጥር 11፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በሀገር አቀፍ ደረጃ የተከበረው የጥምቀት በዓል አዲስ አበባን ጨምሮ በሁሉም የሀገሪቱ አካባቢዎች በስኬት ተጠናቅቋል አለ ፌደራል ፖሊስ።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አማኞች ዘንድ በመላው ሀገሪቱ በታላቅ ድምቀት የተከበረው የከተራና የጥምቀት በዓል በስኬት እንዲጠናቀቅ ‎የፌደራል ፖሊስ ከሌሎች የፀጥታና ደኅንነት አካላት ጋር በመቀናጀት በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የታገዘ ሰፊ የሰው ኃይል በማሰማራት ተገቢውን የፀጥታ ሥራ በማከናወን ኃላፊነቱን ተወጥቷል።

የተሰጣቸውን ሀገራዊ ተልዕኮ መሠረት በማድረግ የሕዝቡን ሰላምና ደኅንነት በማስቀደም ከከተራ ጀምሮ በተለያዩ አካባቢዎች የተጠናከረ ጥበቃ በማከናወን በዓሉ በስኬት እንዲጠናቀቅ ኃላፊነታቸውን በብቃት ለተወጡ የፀጥታና ደኅንነት ተቋማት አመራሮችና አባላት የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ምስጋና አቅርቧል።

እንዲሁም ለፀጥታና ደኅንነት አካላት አስፈላጊውን ትብብርና ድጋፍ በማድረግ የበኩላቸውን ድርሻ ያበረከቱትን የሃይማኖት አባቶች፣ የበዓሉ አስተባባሪዎች፣ የእምነቱ ተከታዮች እና ወጣቶች አመስግኗል።

በነገው ዕለት የሚከበረው ቃና ዘገሊላ በዓልም በስኬት እንዲጠናቀቅ ሕብረተሰቡ ትብብሩን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርቧል።

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation

Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting

Facebook https://web.facebook.com/fanasport

Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate

Telegram t.me/fanatelevision

Telegram https://fanamc.com/amharic/

Website www.fanamc.com

TikTok www.tiktok.com/@fana_television

WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29

Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment

TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment

Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!