ስፓርት

ማንቼስተር ሲቲ የማርክ ጉሂን ዝውውር ይፋ አደረገ

By Yonas Getnet

January 19, 2026

አዲስ አበባ፣ ጥር 11፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የተከላካይ መስመር ተጫዋቹ ማርክ ጉሂ ወደ ማንቼስተር ሲቲ ያደረገውን ዝውውር ክለቡ ይፋ አድርጓል።

የክርስታል ፓላስ የኋላ ደጀን የነበረው እንግሊዛዊው ተጫዋች ጉሂ በፕሪሚየር ሊግ ውስጥ ከሚገኙ ወጥ እና አስተማማኝ ከሚባሉ ተከላካዮች ተርታ መመደብ የቻለ ተጫዋች ነው።

የ25 ዓመቱ የመሃል ተከላካይ ተጫዋቹ በሲቲዎች ቤት ለ5 ዓመታት ከግማሽ የሚያቆየውን የረጅም ዓመት ውል ተፈራርሟል።

ሊቨርፑል እና ባየር ሙኒክን ጨምሮ በበርካታ ታላላቅ ክለቦች ሲፈለግ የነበረው ጉሂ በማንቼስተር ሲቲ በዓመት 15 ነጥብ 6 ሚሊየን ፓውንድ ክፍያ እንደሚያገኝ ተመላክቷል።