አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 16 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የመከላከያ አዛዥነትና ስታፍ ኮሌጅ ለ14ኛ ዙር በወታደራዊ አመራርነት ያሰለጠናቸውን ከፍተኛ መኮንኖች አስመረቀ፡፡
በስነ ስርዓቱ ላይ የጦር ሀይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጀነራል አደም መሀመድ ተመራቂዎች የሀገራቸውን ሉዓላዊንትና የህዝባቸውን ደህንነት ለመጠበቅ ወታደራዊ አመራሮች በዕውቀት ላይ ተመስርተው ሀገርን እና ህዝብን ማገልገል እንደሚጠበቅባቸው ገልፀዋል፡፡