የሀገር ውስጥ ዜና

በኦሮሚያ ክልል የመንግሥትና ፓርቲ አፈጻጸም ግምገማ ተጀመረ

By Yonas Getnet

January 21, 2026

አዲስ አበባ፣ ጥር 13፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በኦሮሚያ ክልል የመንግሥትና ፓርቲ ስራ አፈጻጸም ግምገማ ተጀምሯል።

የ2018 በጀት ዓመት 2ኛ ሩብ ዓመት የመንግሥት እና የፓርቲው አፈፃፀም ግምገማ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳን ጨምሮ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት በአዳማ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።

ርዕሰ መስተዳድሩ በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ በክልሉ የተገኙ ስኬቶችን አጠናክሮ በማስቀጠል እና የተስተዋሉ ድክመቶችን በማረም የተሻለ ውጤት ለማምጣት መስራት ይገባል።

በተለይም ሰላም እና መረጋጋት፣ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ፣ የዜጎች የቁጠባ ባህልን ማሳደግ፣ መልካም አስተዳደር፣ ቀልጣፋ አገልግሎት እና ሌሎች መስኮች ላይ ትኩረት ሊሰጣቸው እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

በሚልኪያስ አዱኛ