የሀገር ውስጥ ዜና

ምርጫ ቦርድ ለቀጣዩ ሀገር አቀፍ ምርጫ የመራጮች ምዝገባ ሰነዶች ህትመትና የቁሳቁሶች ግዥ ጀመረ

By Tibebu Kebede

December 19, 2019

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 8፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለቀጣዩ ሀገር አቀፍ ምርጫ የሚውል የመራጮች ምዝገባ ሰነዶች ህትመትና የቁሳቁሶች ግዥ መጀመሩን አስታወቀ።

ምርጫ ቦርድ ለቀጣዩ ሀገራዊ ምርጫ ከሚያደርጋቸው ዝግጅቶች መካከል አንዱ የሆነውን የመራጮችን ምዝገባ ዘመናዊ እና ተአማኒ የሚያደርግ የህትመት ስራ እንዲጀመር በትላንትናው እለት በዱባይ ስምምነት ተፈራርሟል።