አዲስ አበባ፣ ጥር 13፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ2018 ሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 16ኛ ሳምንት መርሐ ግብር አዳማ ከተማ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን 3 ለ 2 አሸንፏል።
በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ቀን 9 ሰዓት ላይ በተደረገው ጨዋታ የአዳማ ከተማን ግቦች አህመድ ሁሴን (በፍጹም ቅጣት ምት)፣ ቢንያም አይተን እና አቡበከር ሳኒ አስቆጥረዋል።
አዲስ ግደይ እና ሳይመን ፒተር የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ግቦች ከመረብ አሳርፈዋል።
በሊጉ ቀደም ብሎ ቀን 7 ሰዓት ላይ በአዲስ አበባ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ እና ሸገር ከተማ 1 ለ 1 አቻ ተለያይተዋል።