የሀገር ውስጥ ዜና

በውሃ ሃብት ዘርፍ በተከወኑ ተግባራት በቀጣናው ፍትሃዊ ተጠቃሚነት እውን እየሆነ ነው – ሃብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር)

By abel neway

January 22, 2026

አዲስ አበባ፣ ጥር 14፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ባለፉት የለውጥ ዓመታት በውሃ ሃብት ዘርፍ ላይ በተከናወኑ ተግባራት በቀጣናው ፍትሃዊ ተጠቃሚነት እውን እየሆነ ነው አሉ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ሃብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር)፡፡

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የ2018 በጀት ዓመት የ6 ወራት አፈጻጸም ግምገማ መድረክ በነቀምቴ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡

ሚኒስትሩ በዚሁ ወቅት እንዳሉት÷ ኢትዮጵያ ያላትን ሃብት በአግባቡ አውቃና ተጠቅማ እንድትለማ በርካታ ሥራዎች እየተሰሩ ነው፡፡

በዚህም ባለፉት የለውጥ ዓመታት በውሃ ሃብት ዘርፍ በተከናወኑ አበረታች ተግባራት በቀጣናው ፍትሃዊ ተጠቃሚነትን እውን ማድረግ ተችሏል ነው ያሉት፡፡

በየዓመቱ በሕዝብ ንቅናቄ የሚከወኑ የአካባቢ ጥበቃና የአረንጓዴ አሻራ ሥራዎች ለውጥ ማምጣታቸውን አስረድተዋል፡፡

በመድረኩ በውሃና ሳኒቴሽን ዘርፍ ፣ በውሃ ሀብት አስተዳደርና ኢነርጂ ዘርፎች በግማሽ ዓመቱ የነበሩ የዕቅድ ክንውን እና አፈፃፀሞች እየተገመገሙ ሲሆን÷ የክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ተሞክሮ ቀርቧል፡፡

በጎህ ንጉሱ