ስፓርት

ኢትዮጵያ መድን እና ድሬዳዋ ከተማ አቻ ተለያዩ

By abel neway

January 22, 2026

አዲስ አበባ፣ ጥር 14፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ16ኛ ሳምንት የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ኢትዮጵያ መድን እና ድሬዳዋ ከተማ ያለምንም ግብ አቻ ተለያይተዋል፡፡

ቀን 7 ሰዓት ላይ በአዲስ አበባ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ሁለቱም ቡድኖች ግብ ሳያስቆጥሩ ወጥተዋል፡፡

ኢትዮጵያ መድን ያለፉትን ሁለት ተከታታይ ጨዋታዎች አቻ ሲለያይ ድሬዳዋ ከተማ በበኩሉ ያለፉትን አምስት ጨዋታዎች ማሸነፍ አልቻለም፡፡

የሊጉ ጨዋታ በዚሁ ስታዲየም ሲቀጥል ቀን 10 ሰዓት ላይ መቻል ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡

በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ደግሞ ቀን 10 ሰዓት ላይ ሲዳማ ቡና ከኢትዮጵያ ቡና ይገናኛሉ፡፡