ስፓርት

ሲዳማ ቡና እና መቻል አሸነፉ

By sosina alemayehu

January 22, 2026

አዲስ አበባ፣ ጥር 14፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ16ኛ ሳምንት የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና ኢትዮጵያ ቡናን 3 ለ 0 አሸንፏል፡፡

ቀን 10 ሰዓት ላይ በአዲስ አበባ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ የሲዳማ ቡናን የማሸነፊያ ግቦች ብለስ ናጎ ፣ ዮሴፍ ዮሀንስና ፍራኦል መንግሥቱ አስቆጥረዋል።

በሌላ በኩል መቻል ቅዱስ ጊዮርጊስን 2 ለ 0 በሆነ ውጤት ሲያሸንፍ ሁለቱንም የመቻልን ግቦች ፈቱዲን ጀማል ከመረብ አሳርፏል።

ቀደም ሲል በተደረገ የሊጉ ጨዋታ ኢትዮጵያ መድን እና ድሬዳዋ ከተማ ያለምንም ግብ በአቻ ውጤት ተለያይተዋል፡፡