አዲስ አበባ፣ ጥር 15፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው የኢፌዲሪ አየር ኃይል 90ኛ ዓመት ክብረ በዓልን ምክንያት በማድረግ በተሰናዳው የአቪዬሽን ኤክስፖ 2026 ይፋዊ የመክፈቻ መርሐ ግብር ተካሂዷል።
ኤክስፖው “የወደፊቱን የአቪዬሽን አቅም በጋራ እንገባ” በሚል መሪ ሐሳብ የተዘጋጀ መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት መረጃ አመላክቷል።
ኢትዮጵያ ለአቪዬሽን እና ኤሮስፔስ ልማት፣ ዓለም አቀፍ ትብብርን በማጠናከር እና ሀገሪቱን በአቪዬሽን ልማት የቀጣናው እና አኅጉሩ የፈጠራ፣ የክህሎት ልማት እና የዘላቂ እድገት ማዕከል ማድረግ ላይ ያላትን ጽኑ አቋም እና ተግባር እንደሚያሳይም ተገልጿል።