የሀገር ውስጥ ዜና

በጠበላ ከተማ በትራፊክ አደጋ የአንድ ቤተሰብ አባላት የሆኑ 2 ሰዎች ሕይወት አለፈ

By Hailemaryam Tegegn

January 23, 2026

አዲስ አበባ፣ ጥር 15፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወላይታ ዞን ጠበላ ከተማ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የአንድ ቤተሰብ አባላት የሆኑ ሁለት ሰዎች ሕይወት አልፏል፡፡አደጋው ከጠበላ ከተማ ወደ ሶዶ ሲጓዝ የነበረ የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ በተቃራኒ መንገድ ሲጓዝ ከነበረ በባለሁለት እግር ተሽካርካሪ ጋር በመጋጨቱ ነው የተከሰተው፡፡በዚህም በባለሁለት እግር ተሽካርካሪ ሲጓዙ የነበሩ ባልና ሚስት ሕይወታቸው ማለፉን የክልሉ ፖሊስ የሕዝብ ግንኙነትና ገጽታ ግንባታ ዳይሬክተር ም/ኮማንደር አሸናፊ ሃይሌ ለፋና ዲጂታል ተናግረዋል፡፡በአደጋው ከሟቾች በተጨማሪ የአካል ጉዳት የደረሰባቸው ዜጎች መኖራቸውን ጠቅሰው ÷ ተጎጂዎች በአቅራቢያ በሚገኙ ሆስፒታሎች የሕክምና እርዳታ እያገኙ ነው ብለዋል፡፡በተፈጠረው አደጋ የደረሰው ተጨማሪ ጉዳትና የአደጋው መንስኤ እየተጣራ መሆኑንም ነው ያመላከቱት፡፡በመላኩ ገድፍ