አዲስ አበባ፣ ጥር 15፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ የኢትዮጵያ የከተሜነት ጉዞ ብርቱ እንደሆነ ትልሙን፣ ተግባሩንና ቀጣይ መዳረሻውን እየተመለከትን ነው አሉ፡፡
ፕሬዚዳንቱ የጎንደር አብያተ መንግስታትን ጨምሮ በከተማዋ የሚገኙ ታሪካዊ ስፍራዎችንና የልማት ስራዎችን ጎብኝተዋል፡፡
ፕሬዚዳንት ታዬ በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፥ የኢትዮጵያ የከተሜነት ጉዞ እየተገለጠ ነው ብለዋል፡፡
ይህ ጉዞ ብርቱ እንደሆነ ትልሙን፣ ተግባሩንና ቀጣይ መዳረሻውን እየተመለከትን ነው ሲሉ በመልዕክታቸው ገልጸዋል፡፡
ከተሞች ቅርስና ጥሪታቸውን ከዘመናዊነት ጋር ሲያዋህዱና ሲያስማሙ የዕውቀት፣ የሥራ፣ የልማት፣ የሰላም አምባና መቅረዝ ይሆናሉ ነው ያሉት፡፡