ቢዝነስ

ለተኪ ምርት የተሰጠው ትኩረት ዘርፈ ብዙ ውጤት እያመጣ ነው

By Mikias Ayele

January 24, 2026

አዲስ አበባ፣ ጥር 16፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢንዱስተሪ ሚኒስቴር ለተኪ ምርት የተሰጠው ትኩረት ዘርፈ ብዙ ውጤት እያመጣ ነው አለ፡፡

የሚኒስቴሩ የ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ስድስት ወራት ዕቅድ አፈፃጸም መድረክ በአርባ ምንጭ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል፡፡

የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል በመድረኩ እንዳሉት÷ በበጀት ዓመቱ ተኪ ምርቶችን በማምረት 3 ነጥብ 4 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር ማዳን ተችሏል።

ለተኪ ምርት የተሰጠው ትኩረት ዘርፈ ብዙ ውጤት እያመጣ መሆኑን ገልጸው÷ መንግሥት ከውጭ በሚገቡ ምርቶች ላይ ያለውን ጥገኝነት ለመቀነስና የሀገር ውስጥ ምርትን ለማሳደግ እየሰራ እንደሚገኝ አስረድተዋል።

በዚህም የሀገር ውስጥ አቅምን ለመገንባት 96 ምርቶች ተለይተው የመተካት ስራ እየተሰራ መሆኑን ገልጸው፤ በተኪ ምርት የውጭ ምንዛሪ እጥረትን መቅረፍ፣ የሥራ ዕድል መፍጠር እና ዜጎች በተመጣጣኝ ዋጋ ምርት እንዲያገኙ ማስቻሉን ተናግረዋል።

ተኪ ምርትን የማምረት ሥራ ቀጣይነት ያለው ዕድገት እያሳየ መምጣቱንም ጠቁመው÷ ውጤቱን ይበልጥ ለማጠናከር ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት እንደሚሠራ አረጋግጠዋል።

በአረጋዊ ሐየሎም