ቢዝነስ

ኢትዮጵያ እና የዓለም የኢኮኖሚ ፎረም ይበልጥ ተቀራርበው ለመስራት ተስማሙ

By Hailemaryam Tegegn

January 24, 2026

አዲስ አበባ፣ ጥር 16፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ እና የዓለም የኢኮኖሚ ፎረም የኢንቨስትመንትና የልማት አጋርነታቸውን በማጠናከር ይበልጥ ተቀራርበው ለመስራት ተስማምተዋል፡፡

በገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሺዴ የተመራው የኢትዮጵያ ከፍተኛ ልዑክ በስዊዘርላንድ ዳቮስ በተካሄደው የዓለም የኢኮኖሚ ፎረም ላይ ያደረገውን ስኬታማ ተሳትፎ አጠናቅቋል፡፡

ሚኒስትሩ ከመድረኩ ጎን ለጎን ከዓለም የኢኮኖሚ ፎረም ፕሬዚዳንት ቦርጌ ብሬንዴ ጋር የሁለቱን ወገኖች አጋርነት ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡

ፎረሙ ኢትዮጵያ ከዓለምአቀፍ አጋር አካላት ጋር በቴክኖሎጂ ልማትና ዘርፉን በገንዘብ በመደገፍ ዙሪያ እንድትመክር ያስቻለ መሆኑን ጠቅሰው፥ ለፎረሙ አዘጋጆች ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ሁለቱ ወገኖች የኢንቨስትመንትና የልማት አጋርነታቸው በማጠናከር ይበልጥ ተቀራርበው ለመስራት ከስምምነት ደርሰዋል፡፡

በገንዘብ ሚኒስትሩ የተመራው የኢትዮጵያ ልዑክ በ2026 የዓለም ኢኮኖሚክ ፎረም ተሳትፎውን በተሳካ ሁኔታ አጠናቅቋል፡፡