ስፓርት

አትሌት ሀጎስ ገ/ህይወትና አትሌት ቢቂሌ አንበሴ የ10 ኪ.ሜ የጐዳና ውድድርን አሸነፉ

By abel neway

January 25, 2026

አዲስ አበባ፣ ጥር 17፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) አትሌት ሀጎስ ገ/ህይወት እና አትሌት ቢቂሌ አንበሴ የ1ኛው የኢትዮጵያ 10 ኪሎ ሜትር የጐዳና ውድድርን አሸንፈዋል።

ዛሬ ማለዳ በሐዋሳ ከተማ በተደረገው የ10 ኪሎ ሜትር የጐዳና ውድድር በወንዶች አትሌት ሀጎስ ገ/ህይወት በቀዳሚነት አጠናቅቋል።

አትሌት ሀጎስ ውድድሩን ለማጠናቀቅ 28 ደቂቃ 2 ሰከንድ ከ94 ማይክሮ ሰከንድ ፈጅቶበታል።

አትሌት ገመቹ ዲዳ ሁለተኛ እንዲሁም አትሌት አሊ ቃሲም ሶስተኛ በመሆን ውድድሩን ጨርሰዋል፡፡

በሴቶች ምድብ በተደረገ የ 10 ኪሎ ሜትር የጐዳና ላይ ውድድር ደግሞ አትሌት ቢቂሌ አንበሴ በቀዳሚነት አጠናቅቃለች፡፡

አትሌቷ ውድድሩን በአንደኝነት ለማጠናቀቅ 32 ደቂቃ 24 ሰከንድ ከ16 ማይክሮ ሰከንድ የወሰደባት ሲሆን÷ አትሌት ጉተኒ ሻንቆ 2ኛ እንዲሁም አትሌት ሰውሀረግ ሀይማኖት 3ኛ በመሆን ወድድሩን አጠናቅቀዋል።

በርካታ ታዋቂ አትሌቶች የተካተቱበት የኢትዮጵያ 10 ኪሎ ሜትር የጐዳና ውድድር በወንድ 109 ፣ በሴቶች 64 በአጠቃላይ 173 አትሌቶች መሳተፋቸው ተመላክቷል፡፡

በሌዊ በለጠ