ስፓርት

የአርሰናል የቀድሞ ተጫዋች ባካሪ ሳኛ በአዲስ አበባ..

By abel neway

January 25, 2026

አዲስ አበባ፣ ጥር 17፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ፈረንሳዊው የአርሰናል እና የማንቸስተር ሲቲ የቀድሞ ተጫዋች ባካሪ ሳኛ አዲስ አበባ ይገኛል፡፡

አንጋፋው ተጫዋች የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከማክሮን የትጥቅ አምራች ድርጅት ጋር የሚያደርገው የሁለትዮሽ ስምምነት አካል መሆኑ ተመላክቷል።

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከግብፅ ጋር ያደረገውን ጨዋታ ተመልክቻለሁ ያለው ሳኛ÷ ኢትዮጵያ ጥሩ ብሔራዊ ቡድን አላት፤ የዚህ አካል ሆኜ አዲስ አበባ በመምጣቴ ደስተኛ ነኝ ብሏል፡፡