ስፓርት

ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ሀዲያ ሆሳዕናን 2 ለ 1 አሸነፈ

By Adimasu Aragawu

January 25, 2026

አዲስ አበባ፣ ጥር 17፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ17ኛ ሳምንት የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ሀዲያ ሆሳዕናን 2 ለ 1 አሸንፏል።

ቀን 7 ሰዓት ላይ በአዲስ አበባ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ የወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲን ግቦች እንዳልካቸው ጥበቡ እና ቃለአብ ውብሸት (በራሱ ላይ) አስቆጥረዋል።

በጨዋታው ሀዲያ ሆሳዕናን ከመሸነፍ ያልታደገችውን ግብ ደስታ ዋሚሾ ከመረብ አሳርፏል።

የሊጉ ጨዋታ ቀጥሎ ሲካሄድ ቀን 10 ሰዓት ላይ በተመሳሳይ ስታዲየም አርባ ምንጭ ከተማ ከፋሲል ከነማ ይጫወታል።

እንዲሁም በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም 9 ሰዓት ላይ አዳማ ከተማ እና መቐለ 70 እንደርታ ሲገኛኙ÷ በተመሳሳይ ሜዳ አመሻሽ 12 ሰዓት ላይ ባህር ዳር ከተማ እና ሀዋሳ ከተማ ይገናኛሉ።