አዲስ አበባ፣ ጥር 17፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ17ኛ ሳምንት የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ፋሲል ከነማ አርባ ምንጭ ከተማን 3 ለ 2 አሸነፈ።
በጨዋታው የፋሲል ከነማን ግቦች ቃልኪዳን ዘላለም (2) እና ናትናኤል ገብረጊዮርጊስ ሲያስቆጥሩ÷ የአርባምንጭ ከተማን ግቦች ታምራት ኢያሱ እና ጸጋየ አበራ (በፍጹም ቅጣት ምት) ከመረብ አገናኝተዋል።
ቀደም ሲል በተደረጉ ጨዋታዎች አዳማ ከተማ እና መቐለ 70 እንደርታ ያለ ምንም ግብ አቻ ሲለያዩ÷ ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ሀዲያ ሆሳዕናን 2 ለ 1 አሸንፏል።
የሊጉ መርሐ ግብር ቀጥሎ ሲካሄድ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም አመሻሽ 12 ሰዓት ላይ ባሕር ዳር ከተማ እና ሀዋሳ ከተማ ይገናኛሉ።