አዲስ አበባ፣ ጥር 17፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ23ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ መርሐ ግብር ቼልሲ ክሪስታል ፓላስን 3 ለ 1 አሸንፏል።
አመሻሽ 11፡30 ላይ በክሪስታል ፓላስ ሜዳ በተደረገው ጨዋታ የቼልሲን ግቦች ኤስቴቫኦ፣ ጆአ ፔድሮ እና፣ ኤንዞ ፈርናንዴዝ (በፍጹም ቅጣት ምት) ሲያስቆጥሩ÷ ክሪስ ሪቻርድስ የክሪስታል ፓላስን ብቸኛ ግብ ከመረብ አሳርፏል።
የለንደኑ ክለብ ቼልሲ ጨዋታውን ማሸነፉን ተከትሎ በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ አራተኛ ላይ ተቀምጧል።
በተመሳሳይ ሰዓት ላይ በተደረገው የኒውካስል እና አስቶንቪላ ጨዋታ በአስቶንቪለ 2 ለ 0 አሸናፊነት ተጠናቅቋል።
በጨዋታው የአስቶንቪላን ግቦች ኤሚሊያኖ ቡኤንዲያ እና ኦሊ ዋትኪንስ ከመረብ አሳርፈዋል።
እንዲሁም ኖቲንግሀም ፎረስት ብሬንት ፎርድን 2 ለ 0 ሲያሸንፍ÷ ግቦቹን ኢጎር ጄሱስ እና ታይዎ አዎኒዪ አስቆጥረዋል።
የሳምንቱ ተጠባቂ የሆነው የአርሰናል እና የማንቼስተር ዩናይትድ ጨዋታ ምሽት 1 ሰዓት ከ 30 ላይ ይደረጋል።