የሀገር ውስጥ ዜና

የአየር ኃይል ጉዞ ከድልና ጀግንነት ባለፈ በፈጠራና ቴክኖሎጂ ልዕልና የታጀበ ነው – ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

By Yonas Getnet

January 26, 2026

አዲስ አበባ፣ ጥር 18፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ አየር ኃይል የ90 ዓመታት ጉዞ በድልና በጀግንነት ብቻ የተገደበ አይደለም፤ በፈጠራና የቴክኖሎጂ ልዕልና ውጤትም ጭምር እንጂ አሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷ በአየር ኃይል ዋና መሥሪያ ቤት በተከፈተው ዓለም አቀፍ የአየር ኃይል ኤክስፖ ዛሬ ተዘዋውረን የተመለከትነው እውነትም ይሄንኑ የሚያረጋግጥ ነው ብለዋል።

በኤክስፖው የተመለከትናቸው የወታደራዊ ቴክኖሎጂ ውጤቶች የኢትዮጵያን የሩቅ ዘመን የልዕልና ህልም በተጨባጭ በቅርቡ እንደምናሳካው ማረጋገጫዎች ናቸው ሲሉም ተናግረዋል።