አዲስ አበባ፣ ጥር 20፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ከአሜሪካ ምክትል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክርስቶፈር ላንዳው ጋር ተወያይተዋል።
በውይይታቸውም ኢትዮጵያና አሜሪካ ያላቸውን የሁለትዮሽ ግንኙነት ይበልጥ ማጠናከር በሚችሉባቸው ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡
በተጨማሪም ሁለቱ ወገኖች በቀጣናዊ የጋራ ጉዳዮች ላይ ሃሳብ መለዋወጣቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለፋና ዲጂታል ገልጿል፡፡