የሀገር ውስጥ ዜና

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከአሜሪካ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና ከሀገሪቱ የአፍሪካ እዝ አዛዥ ጋር ተወያዩ

By Abiy Getahun

January 28, 2026

አዲስ አበባ፣ ጥር 20፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከአሜሪካ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክሪስቶፈር ቲ ላንዳው እና ከአሜሪካ የአፍሪካ እዝ አዛዥ ጄነራል ዳግቪን አንደርሰን ጋር ተወያይተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ በጽሕፈት ቤታችን ከተገኙት የአሜሪካ ረዳት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክሪስቶፈር ቲ ላንዳው እና የአሜሪካ የአፍሪካ እዝ አዛዥ ጄነራል ዳግቪን አንደርሰን ጋር ተወያይተናል ብለዋል።

ቀጣይነት ያለው ትብብር እና መከባበርን አፅንዖት ለሰጠው ደማቅ እና ገንቢ ውይይታችን ምስጋናዬን አቀርባለሁ ሲሉም ገልጸዋል።