አዲስ አበባ፣ ጥር 22፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ2018 የመጀመሪያዎቹ ሁለት ሩብ ዓመታት አጠቃላይ የስንዴ ምርት 126 ነጥብ 69 ሚሊየን ኩንታል ደርሷል አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማሕበራዊ ትስስር ገፃቸው ባስተላለፉት መልዕክት÷ የኢትዮጵያ የስንዴ ፕሮግራም ምርታማነትን በመጨመር፣ የመስኖ ሥርዓትን በማስፋት፣ የዘር አቅርቦት ሥርዓትን በማጠናከር ብሎም በዋና ዋና አካባቢዎች አነስተኛ አርሶ አደሮችን በመደገፍ የሀገራችንን ራስን የመቻል ጉዞ ግብ ላይ የተመሠረተ ነው ብለዋል።
በ2018 የመጀመሪያዎቹ ሁለት ሩብ ዓመታት አጠቃላይ የስንዴ ምርት 126 ነጥብ 69 ሚሊየን ኩንታል መድረሱን ገልጸው÷ ይኽም የመስኖ ስንዴ ምርትን ሳይጨምር እንደሆነ አመልክተዋል።
አርሶ አደሮቻችንን ማድነቅ እና ማመስገን እፈልጋለሁ፤ ይኽንኑ የሥራ ጽናት ቀጥሉበት ሲሉም አስገንዝበዋል።