ቢዝነስ

አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ የመለያ (ብራንድ) ለውጥ አደረገ

By Melaku Gedif

January 30, 2026

አዲስ አበባ፣ 22 ጥር፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) አንበሳ ባንክ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች በአዳዲስ ቴክኖሎጂዎች ለማቀላጠፍ የሚያስችል የመለያና የስያሜ ለውጥ አድርጌያለሁ አለ።

ባንኩ የስያሜና የሎጎ ለውጥ ያደረገበትን አዲስ ብራንድ ይፋ አድርጓል።

ከዚህ ቀደም “አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ” የሚለው የባንኩ ስያሜ አንበሳ ባንክ በሚል መተካቱን ባንኩ ይፋ አድርጓል፡፡

የአንበሳ ምስል የነበረው ሎጎውን ወደ ጭረት በመቀየር መሪ ቃሉም “እንጀምረው” ማለቱ ይፋ አድርጓል።

የአንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ የዳሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ አለሙ አስፋው፤ ባንኩ  ዲጂታል ቴክኖሎጂን በማቀላጠፍ ተገቢውን የፋይናንስ አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

የዚሁ አንድ አካል የሆነውን የባንኩ አዲስ መለያን (ብራንድ) ይፋ ማድረጉን የጠቆሙት ሰብሳቢው፤ አዲሱ መለያ ቀጣዩን የአንበሳ ባንክ የስኬት ጉዞ የሚያመላክተ ነው ብለዋል።

አዲሱ መለያ አንበሳ ባንክ ለደንበኞች የሚሰጠውን አገልግሎት ዘመኑን የዋጀ፣ በቴክኖሎጂ የዳበረ እንሆን የሚያግዝ ነውም ብለዋል።

የባንኩ ፕሬዚዳንት አቶ ዳንኤል ተከስተ በበኩላቸው፤ የመለያ (ብራንድ) ለውጡ ከባንኩ  ታሪካዊ አወቃቀር የተሳሰረ ነው ብለዋል።

“አዲሱ መለያ የሎጎ ቅየራ ብቻ ሳይሆን ባንኩ ስትራተጂካዊ ‘ፖዝሽን’ ለውጥ ማድረጉ የሚጠቁም ታሪካዊ ምዕራፍ ነው” ብለዋል።

በዓድዋ ድል መታሰቢያ አዳራሽ ባካሄደው የማስተዋወቅ መርሐ ግብር፤ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ አቶ ጌታቸው ረዳ፣ የብሄራዊ ባንክ ምክትል ገዢ አቶ ሰሎሞን ደስታ የአንበሳ ባንክ ዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ አቶ አለም አስፋው እና የባንኩ ፕሬዝዳንት አቶ ዳንኤል ተከስተ ተገኝተዋል።

በገብረማሪያም ወ/ገሪማ