አዲስ አበባ፣ ጥር 23፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በተያዘው በጀት ዓመት ባለፉት 6 ወራት ከግብርና ምርቶች 2 ቢሊየን ዶላር ገቢ ተገኝቷል አለ የግብርና ሚኒስቴር።
ሚኒስቴሩ የ2018 በጀት ዓመት 6 ወራት ዕቅድ አፈፃፀሙን በአዳማ ከተማ እየገመገመ ይገኛል።
የግብርና ሚኒስትር አዲሱ አረጋ በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ ባለፉት 6 ወራት እንደ ሀገር በግብርናው ዘርፍ ውጤታማ ስራዎች ተከናውኗል።
ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ በተሰራው ሥራም 2 ቢሊየን ዶላር ገቢ ማግኘት እንደተቻለ አመልክተዋል።
ወደ ግብርና ሜካናይዜሽን ለመሸጋገር እየተሰራ ባለው ስራም ሰፋፊ ውጤቶች መመዝገባቸውን አንስተው÷ እንደ ሀገር የእርሻ ሥራውን ለማዘመን ከ23 ሺህ በላይ ትራክተሮች፣ ከ12 ሺህ በላይ ኮምባይነሮች እና 500 ሺህ የውሃ ፓምፖች ወደ ሥራ ማስገባት መቻሉን ተናግረዋል።
በዚህም ለእርሻ መካናይዜሽን ጉዞ ምቹ መደላደል መፍጠር ተችሏል ብለዋል።
በሰለሞን ይታየው