አዲስ አበባ፣ ጥር 24፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ከዩናይትድ ኪንግደም የኮመንዌልዝ፣ ልማት ጉዳዮች እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ይቬት ኩፐር ጋር ተወያይተዋል፡፡
ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) በጽ/ቤታቸው ከሚኒስትሯ ጋር ባደረጉት ውይይት፥ ረዥም ጊዜ ያስቆጠረውን የሁለቱን ሀገራት ጠንካራ ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማሳደግ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡
በተጨማሪም በቀጣናዊ የሰላምና ጸጥታ ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡