አዲስ አበባ፣ ጥር 24፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ18ኛ ሳምንት የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ፋሲል ከነማ ቅዱስ ጊዮርጊስን 1 ለ 0 አሸንፏል፡፡
ቀን 10 ሰዓት ላይ በአዲስ አበባ ስታዲየም በተደረገ ጨዋታ የፋሲል ከነማ ቶሎሳ ንጉሴ (በራስ ላይ) ባስቆጠራት ብቸኛ ግብ ሶስት ነጥብ ይዞ ወጥቷል።
በዕለቱ በተደረጉ የሊጉ 18ኛ ሳምንት መርሐ ግብሮች መቐለ 70 እንደርታ እና ኢትዮጵያ ቡና 1 ለ 1 በሆነ አቻ ውጤት ሲለያዩ፤ አርባምንጭ ከተማ ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲን 2 ለ 1 አሸንፏል።