የሀገር ውስጥ ዜና

የአዳማ ኢንዱስትሪ ፓርክን የኃይል አቅርቦት አስተማማኝ ለማድረግ…

By Melaku Gedif

February 02, 2026

አዲስ አበባ፣ ጥር 25፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዳማ ኢንዱስትሪ ፓርክን የኃይል አቅርቦት ይበልጥ አስተማማኝ ለማድረግ የሚያስችል የኤሌክትሪክ ኃይል መስመር ዝርጋታ ሥራ ተከናውኗል አለ የኢዮትጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት፡፡

ኢንዱስትሪ ፓርኩ ከዚህ በፊት ከአዋሽ መልካሳ ማከፋፈያ ጣቢያ ኃይል ሲያገኝ የቆየ ሲሆን ÷ የራሱ ብቸኛ መስመር ባለመኖሩ የኃይል መቆራረጥና መዋዠቅ ያጋጥመው እንደነበር ተመላክቷል፡፡

አሁን ላይም ከአዳማ ቁጥር 3 የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ በቀጥታ አራት ባለ 33 ኪሎ ቮልት መካከለኛ መስመሮች ለፓርኩ በመዘርጋት አስተማማኝ የኤሌክትሪክ ኃይል እንዲኖረው መደረጉ ነው የተገለጸው፡፡

የኤሌክትሪክ ኃይል መስመር ዝርጋታው 56 ነጥብ 25 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን ሲሆን ÷ በዚህም 800 ባለ 12 ሜትር እና 500 ባለ 14 ሜትር አጠቃላይ 774 የኮንክሪት ምሰሶዎች ተከላ ተከናውኗል፡፡

40 ሜጋ ዋት ኃይል ለፓርኩ በቀጥታ ማቅረብ የሚያስችል ዓቅም ያለው ማከፋፈያ ጣቢያው ÷ አምራች ኢንዱስትሪዎቹ አሁን የሚጠቀሙትን የኃይል መጠን በከፍተኛ ሁኔታ ለማሳደግና ተጨማሪ አምራቾችን መሳብ ያስችላል፡፡

በኢንዱስትሪ ፓርኩ ውስጥ ተሰማርተው የሚገኙ የውጭ ባለሃብቶች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን ተከትሎ ያለውን ተጨማሪ የኃይል ፍላጎት ለማሟላት ከፍተኛ አቅም እንደሚሆንም አገልግሎቱ ለፋና ዲጂታል ገልጿል፡፡

በመላኩ ገድፍ