አዲስ አበባ፣ ጥር 25፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ከሳዑዲ ዓረቢያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ልዑል ፋይሰል ቢን ፈርሃን አል ሳዑድ ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸውም የኢትዮጵያ እና ሳዑዲ ዓረቢያን የሁለትዮሽ ግንኙነት ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡
የሁለቱን ሀገራት ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ግንኙነት በማጎልበት ወደ ላቀ ስትራቴጂካዊ አጋርነት ማሳደግ እንደሚገባ ነው ያስገነዘቡት፡፡
ሚኒስትሮቹ በአፍሪካ ቀንድ ዘላቂ ሰላም እና መረጋጋት ለመፍጠር በቅርበት ለመስራት ስምምነት ላይ መድረሳቸውንም ሚኒስቴሩ ለፋና ዲጂታል ገልጿል፡፡