👉 በግብርና የዚህ ዓመት ዕቅዳችን 7 ነጥብ 3 እድገት እናረጋግጣለን፤ 1 ነጥብ 3 ቢሊየን ኩንታል ምርት እናመርታለን የሚል ነው።
👉 ባለፉት 6 ወራት በተለይ ክረምት ላይ ከፍተኛ ምርት የተገኘበት ዓመት ስለሆነ 6 ወር በሰራነው ሥራ 999 ሚሊየን ኩንታል መሰብሰብ ተችሏል። ይህም ከዓመቱ ዕቅድ 78 በመቶ የሚሸፍን ነው።
👉 በሰብል፣ በአትክልት እና ፍራፍሬ እንዲሁም በጥጥ ምርት የዓመቱን ዕቅድ 79 በመቶ በ6 ወር መሸፈን ተችሏል፤ በሚቀጥሉት 6 ወራትም ይህንን አጠናክረን ከቀጠልን ካሰብነው በላይ ማሳካት እንችላለን።
👉 የፕላን እና ልማት ሚኒስቴር 88 ሺህ የሚጠጉ ኢትዮጵያውያን ከ19 ሺህ በላይ በሚሆኑ ቀበሌዎች በማሰማራት የቤት ለቤት መረጃ የመሰብሰብ ስራ እየተሰራ ሲሆን÷ ይህ ሲጠናቀቅ በርካታ አዳዲስ መረጃዎች እንደምናገኝ ይጠበቃል።
👉 ከዚህ የመረጃ መሰብሰብ ስራ የግብርና ዘርፍን ብንመለከት በኢትዮጵያ፡- • ትራክተር በ2010 ዓ.ም 4 ሺህ 700 ገደማ እንደነበር እና አሁን ላይ ወደ 27 ሺህ 200 አድጓል።
• ኮምባይነር በ2010 ዓ.ም 338 ገደማ የነበረ ሲሆን÷ ዛሬ ላይ 8 ሺህ 700 ኮምባይነር አለ።
• የግለሰብ የውሃ ፓምፕ በ2010 ዓ.ም 6 ሺህ ገደማ የነበረው ወደ 280 ሺህ ከፍ ብሏል።
👉 አጠቃላይ ውጤቱ ሲደርስ የሚገለጽ ቢሆንም በመረጃ አሰባሰቡ በተገኘው መረጃ መሰረት በግለሰብ አርሶ አደሮች ደረጃ በክላስተር እና በቴክኖሎጂ አጠቃቀም የመጣው እድገት ከፍተኛ ነው።
👉 የተፈጥሮ አፈር ማዳበሪያ አጠቃቀም ጋር በተያያዘ ከግብርና ተረፈ ምርቶች ኮምፖስት የማዘጋጀት ልምዱ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መጥቷል።
👉 በአካባቢ ጥበቃ ላይ የተሰራው ስራ፣ የአረንጓዴ ዐሻራ እንቅስቃሴ፣ በሚሊየን ሄክታር የሚጠጉ መሬቶች ወደ እርሻ በመጨመሩ፣ የበጋ እርሻ፣ የሌማት ትሩፋት ኢኒሼቲቮች የግብርና ሂደትን በከፍተኛ ደረጃ አሻሽለዋል።
👉 አሁን ላይ ደግሞ የማዳበሪያ ፋብሪካ በሀገር ውስጥ መስራት ብቻ በቂ አይደለም ብለን በመላው ኢትዮጵያ ተንቀሳቃሽ ላብራቶሪዎች የማዘጋጀት ስራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ።
👉 ይህም እንደ የአካባቢው ምርት እና የመሬት ዓይነት ተስማሚ የሆነ የአፈር ማዳበሪያ ማቅረብ የሚያስችል ጥናቶች እየተጠናቀቀ የሚገኝ ሲሆን÷ በዚህም አሁን ካለው ምርት በእጅጉ እንዲያድግ ያደርጋል።
👉 አሁንም በመጣው በየትኛውም ዘመን ታይቶ የማያውቅ አመርቂ ውጤት ሳንኩራራ ከዚህ በላይ በመስራት ምርታማነት እንዲያድግ መስራት ያስፈልጋል።
በዮናስ ጌትነት