👉 በሀገር ውስጥ የውይይት በር ክፍት ማድረግ አለብን፡፡
👉 ዛሬ ባንዳ የሆነ፥ ከኢትዮጵያ ተቃርኖ የቆመ ሰው ልብ ገዝቶ በቃኝ ካለ ሁሌም ክፍት መሆን አለብን፡፡
👉 በሀገር ጉዳይ ቂም መያያዝ አያስፈልግም፥ ልቤ ታድሷል፣ አእምሮዬ ተቀይሯል ካለ በራችን ክፍት መሆን አለበት፡፡
👉 ይህንንም እያደረግን ቆይተናል፥ ጉዳያችን ኢትዮጵያን የሚጠቅም ከሆነ በይቅርታ ለማለፍ ዝግጁዎች ነን።
👉 በዚህም በተለያዩ ክልሎች የሚገኙ ታጣቂዎች ተመልሰው እየገቡ ይገኛሉ።
👉 ለሰላም ዝግጁ እስከሆነ ድረስ የግል ስሜትን ወደጎን ቶት ለይቅርታ ዝግጁ መሆን ያስፈልጋል።
👉 ብሔራዊ ጥቅም ላይ አሁን ያለው ሁኔታ በጣም ተሻሽሏል።
👉 በተለያዩ አካባቢዎች የሚንቀሳቀሱ ኃይሎች ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅም የተቃረነ እንቅስቃሴን በመቃወም ወደ ሰላም እየመጡ ነው።
👉 በጫካ ሆነው ከመንግስት ጋር ትብብር እያደረጉ የሚገኙት ቁጥራቸው ቀላል የሚባል አይደለም።
በዮናስ ጌትነት