አዲስ አበባ፣ ጥር 27፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የገዳ ሥርዓት ተመራማሪ የነበሩት አስመሮም ለገሰ (ፕ/ር) ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።
አስመሮም (ፕ/ር) የገዳ ሥርዓት እንዲጠበቅ፣ እንዲከበርና በዓለም አቀፍ ደረጃ ዕውቅና እንዲያገኝ የሰሩ በተለይም የኦሮሞ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ እሴቶችና የሰብአዊ መብት ጥበቃ መርሆዎች በጽሑፍ ተመዝግበው ለትውልድ እንዲሸጋገሩ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክተዋል።
በገዳ ሥርዓት ዙሪያ በርካታ መጻሕፍትና የምርምር ሥራዎችን ለንባብ ያበቁት አስመሮም (ፕ/ር)÷ የሥርዓቱን ዴሞክራሲያዊነት በማጉላት ለሰብአዊ መብት መከበርና ለሕዝቦች ክብር በጽናት የታገሉም ሰው ናቸው።
የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ በአስመሮም ለገሰ (ፕ/ር) ህልፈተ ሕይወት የተሰማቸውን ሐዘን ገልጸው÷ ለቤተሰቦቻቸውና ወዳጅ ዘመዶቻቸው መጽናናትን ተመኝተዋል።