አዲስ አበባ፣ ጥር 28፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ለ39ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባኤ ኢትዮጵያ አስፈላጊውን ዝግጅት አጠናቅቃለች አለ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፡፡
የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ አምባሳደር ነቢያት ጌታቸው በዛሬው ዕለት በሰጡት መግለጫ እንዳሉት፥ ጉባኤውን ለማስተናገድ አስፈላጊው የይዘትና የሎጅስቲክስ ዝግጅት ተደርጓል፡፡
የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባኤ የካቲት 7 እና 8 የሚካሄድ ሲሆን፥ የኅብረቱ የስራ አስፈጻሚ ስብሰባ የካቲት 4 እና 5 እንደሚከናወን ተናግረዋል፡፡
ጉባኤ በፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ላይ የኢትዮጵያን ገጽታ ለማስተዋወቅ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንዳለው ገልጸው፥ ኢትዮጵያ ስኬት የተመዘገባበቸውን ተግባራት በተመለከተ ልምዷን እንደምታካፍል ጠቁመዋል፡፡
በዋናነትም በአረንጓዴ አሻራ፣ በስንዴ ልማት፣ በኮሪደር ልማትና በሰውሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ የተገኙ ተጨባጭ ለውጦችን በተመለከተ ልምዷን ታጋራለች ነው ያሉት፡፡
በተጨማሪም የጣልያን-አፍሪካ የመሪዎች ስብሰባ የካቲት 6 በአዲስ አበባ ይካሄዳል ብለዋል፡፡
በአመለወርቅ መኳንንት