የሀገር ውስጥ ዜና

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤ መካሄድ ጀመረ

By Adimasu Aragawu

February 06, 2026

አዲስ አበባ፣ ጥር 29፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የስራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ጉባኤ የቀረቡለትን አራት አጀንዳዎች በማጽደቅ ጉባኤውን እያካሄደ ይገኛል፡፡

የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ቡዜና አልከድር አጀንዳዎች ለምክር ቤቱ ያቀረቡ ሲሆን÷ ምክር ቤቱም የቀረቡለትን አጀንዳዎች አጽድቋል፡፡

ጉባኤው የምክር ቤቱን 5ኛ ዓመት የስራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ጉባኤ ቃለ ጉባኤ አጽድቋል፡፡

የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ አዳነች አቤቤ የአስተዳደሩን የበጀት ዓመቱ ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት በማቅረብ ላይ ናቸው።

በሪፖርታቸውም አዲስ አበባ ግልጽ ከሆነ የብልጽግና እሳቤ የተቀዱ ስትራተጂዎችና ፖሊሲዎች እየተመራች በርካታ ተግባራት ተከናውነዋል ነው ያሉት።

በዚህም በዘመናት መካከል የተመላለስንበትን የድህነት እና የኋላ ቀርነት ታሪክ እንዲሁም ጎስቋላ ገጽታን እየፋቅን ከመጥፎ ጠረን እየራቅን ከድንግዝግዙ እየተላቀቅን አሁን ወደምንገኝበት የተጨበጠ እና ወደሚታይ ብርሃናማ ምዕራፍ ተሸጋግረናል ብለዋል።