አዲስ አበባ፣ ጥር 29፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ የበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ስድስት ወራት በመዲናዋ ለ2 ሺህ 549 ባለሃብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ ተሰጥቷቸዋል አሉ።
ከንቲባዋ ያለፉት ስድስት ወራት የከተማዋ ኢንቨስትመንት እንቅስቃሴን በተመለከተ ለከተማ አስተዳደሩ ምክር ቤት ባቀረቡት ሪፖርት ነው ይህንን የገለጹት።
በዚህም የኢንቨስትመንት ፈቃድ አሰጣጥ ከታቀደው በላይ አፈጻጸም ማሳየቱን ገልጸው÷ 1 ሺህ 750 አዲስ ፈቃድ ለመስጠት ታቅዶ ለ2 ሺህ 549 ባለሃብቶች ፈቃድ መሰጠቱን ተናግረዋል።
162 ማስፋፊያ ፈቃድ እንዲሁም 981 የኢንቨስትመንት ፈቃድ ታድሷል ብለዋል።
በበጀት ዓመቱ በላፉት ስድስት ወራት ለ42 የውጭ ዜጎች የስራ ፈቃድ ተሰጥቷልም ነው ያሉት።