ስፓርት

ማንቼስተር ዩናይትድ ቶተንሀምን አሸነፈ

By Yonas Getnet

February 07, 2026

አዲስ አበባ፣ ጥር 30፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ25ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ማንቼስተር ዩናይትድ ቶትንሃም ሆትስፐርስን 2 ለ 0 አሸንፏል፡፡

በጨዋታው የማንቼስተር ዩናይትድን ግቦች ብሪያን ሙቤሞ እና ብሩኖ ፈርናንዴሽ ከመረብ አሳርፈዋል።

በጨዋታው መጀመሪያው አጋማሽ የቶተንሀም አምበል ክሪስቲያን ሮሜሮ በሰራው ጥፋት በቀጥታ ቀይ ካርድ ከሜዳ መውጣቱን ተከትሎ ቀያዮቹ ሰይጣኖች የበላይነት አግኝተዋል።

በማይክል ካሪክ አሰልጣኝነት ስር ከፍተኛ መነሳሳት እያሳዩ የሚገኙት ዩናይትዶች አራት ተከታታይ ጨዋታዎችን ማሸነፍ ችለዋል።

የሊጉ መርሐ ግብር ቀጥሎ ሲካሄድ ምሽት 12 ሰዓት በኢምሬትስ ስቴዲየም አርሰናል ከሰንደርላንድ የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል።

እንዲሁም በተመሳሳይ ሰዓት ቦርንማውዝ ከአስቶንቪላ፣ በርንሌ ከዌስትሃም ዩናይትደ፣ ፉልሃም ከኤቨርተን እንዲሁም ዎልቭስ ከቼልሲ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡

ኒውካስል ዩናይትድን ከብሬንትፎርድ የሚያገናኘው ጨዋታ ደግሞ ምሽት 1 ሰዓት ከ30 ላይ ይካሄዳል።