አዲስ አበባ፣ የካቲት 2፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ዛሬ በኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የሰው አልባ ፖሊስ አገልግሎት ወይም ስማርት ፖሊስ አገልግሎት አስጀምረዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማሕበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት÷ አገልግሎቱ ዜጎች የፖሊስ አገልግሎትን በተሻለ ፍጥነት እና በቴክኖሎጂ ታግዘው እንዲያገኙ እንደሚያስችላቸው ገልጸዋል።
በተጨማሪም አገልግሎቱ ለፖሊስ ፈጣን ርምጃ ለመውሰድ የሚያስችል እና የወንጀል መከላከል ስራውን የሚያቀላጥፍ ነው ብለዋል።
የዚህ አገልግሎት መጀመር በዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 የህግ አስከባሪ አካላት ብቁና ተወዳዳሪ እንዲሆኑ የተጀመረው የሪፎርም ስራን ውጤታማነት የሚያሳድግ ይሆናልም ነው ያሉት።