ስፓርት

ማንቼስተር ዩናይትድ በሊጉ 5ኛ ተከታታይ ድሉን ለማሳካት…

By sosina alemayehu

February 10, 2026

አዲስ አበባ፣ የካቲት 3፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ26ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር በዛሬው ዕለት አራት ጨዋታዎች ይደረጋሉ፡፡

ምሽት 5 ሰዓት 15 ላይ ዌስትሃም ዩናይትድ በሜዳው ማንቼስተር ዩናይትድን ያስተናግዳል፡፡

በሊጉ ያለፉትን አራት ተከታታይ ጨዋታዎች ማሸነፍ የቻለው ማንቼስተር ዩናይትድ 5ኛ ተከታታይ ድሉን ለማሳካት ወደ ሜዳ ይገባል፡፡

ወራጅ ቀጠና ላይ የሚገኘው ዌስትሃም ዩናይትድ በበኩሉ ተከታታይ ሁለተኛ ጨዋታውን ለማሸነፍ ይፋለማል።

ከእዚህ ጨዋታ አስቀድሞ ምሽት 4 ሰዓት 30 ላይ ቼልሲ በሜዳው ስታምፎርድ ብሪጅ ከሊድስ ዩናይትድ ጋር ጨዋታውን ያደርጋል፡፡

በሊጉ ያለፉትን አራት ተከታታይ ጨዋታዎች ያሸነፈው ቼልሲ አሸናፊነቱን ለማስቀጠል ወደ ሜዳ የሚገባ ይሆናል፡፡

ቶተንሃም ሆትስፐር ከኒውካስል ዩናይትድ እንዲሁም ኤቨርተን ከቦርንማውዝ በተመሳሳይ ምሽት 4 ሰዓት 30 ላይ የሚደረጉ ጨዋታዎች ናቸው፡፡