የሀገር ውስጥ ዜና

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከሳዑዲ ዓረቢያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

By Yonas Getnet

February 11, 2026

አዲስ አበባ፣ የካቲት 4፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሳዑዲ ዓረቢያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ልዑል ፋይሰል ቢን ፋርሃን አል ሳዑድ ጋር ተወያይተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷ ዛሬ የሳዑዲ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ልዑል ፋይሰል ቢን ፋርሃን አል ሳዑድን ተቀብዬ በሁለትዮሽና ባለብዙ ወገን ጉዳዮች ላይ ውጤታማ ውይይት አድርገናል ብለዋል።

‎በውይይታቸውም በዐበይት ዘርፎች ለረዥም ዘመናት የዘለቀውን የሁለቱን ሀገራት ትስስር ማስፋት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ በትኩረት መክረዋል፡፡

እንዲሁም የሀገራቱ የወል ፍላጎት በሆኑ ቀጣናዊ እና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ላይ ያለውን ትብብር በማጠናከር ላይ ያተኮረ እንደነበር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) አመልክተዋል፡፡