ዓለምአቀፋዊ ዜና

የአፍሪካ ህብረት የሥራ አስፈጻሚ ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ተጠናቀቀ

By Yonas Getnet

February 12, 2026

አዲስ አበባ፣ የካቲት 5፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) 48ኛው የአፍሪካ ህብረት የሥራ አስፈጻሚ ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ተጠናቅቋል።

ስብሰባው “ዘላቂ የውሃ አቅርቦትና ደህንነቱ የተጠበቀ የንጽህና አጠባበቅ ሥርዓቶችን ማረጋገጥ፤ ለአጀንዳ 2063 ግቦች ስኬታማነት” በሚል መሪ ሃሳብ ከትናንት ጀምሮ ሲካሄድ ነበር።

የህብረቱ አባል ሀገራት የጋራ ፍላጎት የሆኑ የፖሊሲ ጉዳዮችን የሚያስተባብርና ውሳኔ የሚሰጠው ምክር ቤቱ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ መምከሩ ተገልጿል።

ኢትዮጵያ በስብሰባው ብሔራዊ ጥቅሞቿን የሚያስጠብቁ አጀንዳዎች ማቅረቧ ተገልጿል።

እንደ ቀደመው ሁሉ ለሰላምና ደህንነት መረጋገጥ ሚናዋን እንደምትወጣ ያረጋገጠችው ኢትዮጵያ፤ የራሷን አጀንዳ ከማንፀባረቅ ባሻገር ለአሕጉሪቱ አጀንዳ 2063 መሳካት የበኩሏን ጥረት እያደረገች ትገኛለች።

በሰለሞን በየነ