የሀገር ውስጥ ዜና

የአንጎላ፣ የቦትስዋና እና የቡሩንዲ ፕሬዚዳንቶች አዲስ አበባ ገቡ

By Hailemaryam Tegegn

February 12, 2026

አዲስ አበባ፣ የካቲት 5፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የወቅቱ የአፍሪካ ኅብረት ሊቀመንበር እና የአንጎላ ፕሬዚዳንት ጆአዎ ሎሬንሶ በ39ኛው የኅብረቱ የመሪዎች ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡

በተመሳሳይ የቦትስዋና ፕሬዚዳንት ዱማ ጌዲዮን ቦኮ እና የቡሩንዲ ፕሬዚዳንት ኢቫሪስቴ ንዳይሺሚዬ በመሪዎች ጉባዔው ላይ ለመሳተፍ በዛሬው ዕለት አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡

ፕሬዚዳንቶቹ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር) አቀባበል አድርገውላቸዋል።

39ኛው የኅብረቱ የመሪዎች ጉባዔ “ዘላቂ የውሃ አቅርቦትና ደህንነቱ የተጠበቀ የንጽህና አጠባበቅ ስርዓቶችን ማረጋገጥ፥ ለአጀንዳ 2063 ግቦች ስኬታማነት” በሚል መሪ ሀሳብ በመጪው ቅዳሜ እና እሁድ ይካሄዳል።