የሀገር ውስጥ ዜና

የሕብረቱ መሪዎች ጉባዔ ተሳታፊዎች በኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት አማራጮችን እንዲመለከቱ ጥሪ ቀረበ

By Adimasu Aragawu

February 13, 2026

አዲስ አበባ፣ የካቲት 6፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ ተሳታፊዎች በኢትዮጵያ ያለውን የኢንቨስትመንት አማራጮች እንዲመለከቱ ጥሪ ቀርቧል፡፡

በኢትዮጵያ በሀገር ውስጥ የኢኮኖሚ ማሻሻያ አጀንዳዎች፣ በውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት፣ በዘመናዊ ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች፣ የአፍሪካ እና ዓለም አቀፍ ገበያዎች ያለችግር ተደራሽነት ላይ የተመሰረተ ሥነ ምህዳር መገንባቱ ተገልጿል፡፡

በስትራቴጂካዊ፣ ዘላቂነት ላይ ባተኮረ አመራር በመመራት እና በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ላይ ታዳሽ ኃይል፣ የዲጂታል መሠረተ ልማትን ማስፋፋት እና የተሻሻለ ቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ሰፋፊ ሥራዎች መሰራታቸውም ተመላክቷል።

በተጨማሪም የሰለጠነ የሰው ኃይል በግብርና፣ ማኑፋክቸሪንግ፣ ኢ-ኮሜርስ፣ ማዕድንና ቀጣናዊ የእሴት ሰንሰለቶችን በማጠናከር እና የአፍሪካን የጋራ ብልጽግና በማሳደግ ላይ የተሰሩ ስራዎች ማቅረቧን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

39ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ “ዘላቂ የውሃ አቅርቦትና ደህንነቱ የተጠበቀ የንጽህና አጠባበቅ ስርዓቶችን ማረጋገጥ፤ ለአጀንዳ 2063 ግቦች ስኬታማነት” በሚል መሪ ሐሳብ በመጪው ቅዳሜ እና እሁድ ይካሄዳል።