አዲስ አበባ፣ የካቲት 6፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የሶማሊያው ፕሬዚዳንት ሐሰን ሼክ መሀሙድ በ39ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ እንዲሁም የአፍሪካ ጣሊያን ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገብተዋል።
ፕሬዚዳንቱ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የገቢዎች ሚኒስትር አይናለም ንጉሴ አቀባበል አድርገውላቸዋል።
39ኛው የሕብረቱ የመሪዎች ጉባዔ “ዘላቂ የውሃ አቅርቦትና ደህንነቱ የተጠበቀ የንጽህና አጠባበቅ ስርዓቶችን ማረጋገጥ÷ ለአጀንዳ 2063 ግቦች ስኬታማነት” በሚል መሪ ሐሳብ ነገና ከነገ በስቲያ ይካሄዳል።
በ39ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ እና የጣሊያን አፍሪካ ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ የተለያዩ ሀገራት መሪዎች እና የተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝን ጨምሮ የተቋማት ኃላፊዎች አዲስ አበባ መግባታቸው ይታወቃል።
በመራኦል ከድር