የሀገር ውስጥ ዜና

የኬንያ ፕሬዚዳንት ዊልያም ሩቶ አዲስ አበባ ገቡ

By Melaku Gedif

February 13, 2026

አዲስ አበባ፣ የካቲት 6፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኬንያ ፕሬዚዳንት ዊልያም ሩቶ በ39ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ እንዲሁም የጣሊያን አፍሪካ ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገብተዋል።

ፕሬዚዳንቱ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የማዕድን ሚኒስትር ሃብታሙ ተገኝ (ኢ/ር) አቀባበል አድርገውላቸዋል።

39ኛው የሕብረቱ የመሪዎች ጉባዔ “ዘላቂ የውሃ አቅርቦትና ደህንነቱ የተጠበቀ የንጽህና አጠባበቅ ስርዓቶችን ማረጋገጥ÷ ለአጀንዳ 2063 ግቦች ስኬታማነት” በሚል መሪ ሐሳብ ነገና ከነገ በስቲያ ይካሄዳል።

በ39ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ እና የጣሊያን አፍሪካ ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ የተለያዩ ሀገራት መሪዎች እና የተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝን ጨምሮ የተቋማት ኃላፊዎች አዲስ አበባ መግባታቸው ይታወቃል።