የሀገር ውስጥ ዜና

የአፍሪካ የአቻ ግምገማ ስርዓት ከመቼውም ጊዜ በበለጠ አስፈላጊ ነው – ፕሬዚዳንት ታዬ

By Yonas Getnet

February 13, 2026

አዲስ አበባ፣ የካቲት 6፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአፍሪካ የአቻ ግምገማ ስርዓት መድረክ ከመቼውም ጊዜ በበለጠ አስፈላጊ ነው አሉ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ።

የአፍሪካ የአቻ ግምገማ ስርዓት (APRM) መድረክ ዛሬ በአዲስ አበባ የተለያዩ አፍሪካ ሀገራት መሪዎች እና ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት ተካሂዷል።

በመድረኩ ንግግር ያደረጉት ፕሬዚዳንት ታዬ በማሕበራዊ የትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ አፍሪካ ከዚህ በፊት በርካታ ፈተናዎች ተጋፍጣ ማለፏን አስታውሰዋል።

መጪው ጊዜም ከፈተና ነጻ ሊሆን እንደማይችል በመገንዘብ በትጋት መስራት እንደሚገባ አመልክተዋል።

በፍጥነት እየተለዋወጠ በሚገኘው የዓለም ስርዓት ውስጥ ስትራቴጂካዊ ውድድር ትርጉም ያለው ትብብርን እንደሚያመጣ ጠቅሰዋል።

በዚህ ረገድ የአፍሪካ የአቻ ግምገማ ስርአት መድረክ ከመቼውም ጊዜ በላይ ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል።